“ሳቋማ” በዩቲዩብ ቻናል ፣ በድረ-ገፅ እና በሞባይል አፕሊኬሽን አማካኝነት ተማሪዎችን የሚረዳ መድረካችን ነው። በይማሩ ላይ የ KG-12 STEM ትምህርትን እንዲሁም የቋንቋ ሥልጠናዎችን እየገነባን እንገኛለን ፡፡
እያደግን ስንሄድ የሙያ ትምህርት ፣ የከፍተኛ ትምህርት እና የግል እድገትን የሚያግዙ ሌሎች መድረኮችን እንደምናካትት ተስፋ እናደርጋለን ፡፡
በስትሪሚንግ “streaming” ታዋቂ የሆኑት አፕሊኬሽኖች የሚጠቀሙባቸውን ዘዴዎች ጥቅም ላይ በማዋል አፕሊኬሽናችን ቀላል እና ብዙ ትምህርትዎችን የማስተላለፍ ብቃት ያለው ነው። ያለምንም ችግር ቪዲዮቻችንን ዳውንሎድ በማድረግ እንደፈለጉ መመልከት ይችላሉ።
አፕሊኬሽኑ ከጊዜ ጊዜ የሚሻሻል እና ከድርጅታችን ጋራ አብሮ የሚያድግ ነው።
በማንኛውም ስማርት የመገናኛ መስሪያዎች ሊጎበኝ የሚችል ሲሆን ትምህርትዎችን “ስትሪም” ማድረግ ይችላሉ።
የኢንተርኔት እና የዳታ ስርጭት ኢትዮጵያ ውስጥ አሁንም ተደራሽነት ይጎለዋል። ይሄንን ችግር ለመቋቋም እና የዲጂታል ትምህርትን ለሁሉም ለማድረስ በሌላ አይነት ቴክኖሎጂ እንጠቀማለን።
ትናንሽ ሰርቨርዎችን በተለያዩ ትምህርት ቤትዎች እና ተማሪዎች በሚገኙባቸው ቦታዎች በመግጠም ትምህርታችን ያለ ምንም ኢንተርኔት ዳውንሎድ እንዲደረግ ያስችላል። እነዚህ ሰርቨርዎች አጠቃቀማቸው ቀላል እና በቀላሉ የማይበላሹ ናቸው።