ስለ እኛ

የሳቋማ መምህራን እና ሰራተኞች የሚሰሩት “Education for Ethiopia” / “ትምህርት ለኢትዮጵያ” በተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ስር ተደራጅተው ነው። ሁሌም ቢሆን እናንተን ለማገልገል ዝግጁ ናቸው።

ቡድናችን

ሊና ጌታቸው አየነው

ዳይሬክተር እና መስራች

​ሊና የድርጅቱ መስራች እና ዳይሬክተር ስትሆን አዲስ አበባ ውስጥ ነው ተውልዳ ያደገችው። የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪዎችዋን አሜሪካ በሚገኘው ዬል ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ያጠናቀቀችው በአሁኑ ሰዓት በቻይና ሀገር በቤጂንግ ከተማ ነው የምትኖረው። 

​ክሌሞ ዦን

ዋና የቴክኒክ ኦፊሰር

ክሌሞ ፈረንሳዊ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪውን በሀገሩ በሚገኝ ኤፒቴክ የተሰኘ ዩኒቨርሲቲ ነው ያገኘው። ሁለተኛ ዲግሪውን በቻይና ታዋቂ ከሆነው ቺንግኋ ዩኒቨርሲቲ በኮምፒውተር ሳይንስ አጠናቋል። በቻይና ሀገር በቤጂንግ ከተማ ነው የሚገኘው። 

አሳምነው የራንጎ

የኬሚስትሪ ቪዲዮ ሌክቸረር

አሳምነው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኬሚስትሪ ትምህርትዎች ሌክቸረር ነው። ማስተርስ እና ባችለር ዲግሪዎቹን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ውጤት ያጠናቀቀ ሲሆን ለዚህም የአክሊሉ ለማ የተሰኘው ስኮላርሺፕም ጨምሮ የተለያዩ ሽልማትዎችን ተቀብሏል። 

ቤዛ ኤርሚያስ ዳኜ

የባዮሎጂ ቪዲዮ ሌክቸረር

ቤዛ በ”ማስተርስ ኦፍ ኤዱኬሽን” ትምህርት ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሂውስተን የተመረቀች ሲሆን በቴክሳስ በሚገኙ ትምህርት ቤትዎች ውስጥ የ9ኛ እና የ8ኛ ባዮሎጂ መምህርት ሆና አገልግላለች። የመጀመሪያ ዲግሪዋን ያገኘችው ደግሞ በህንድ ከሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ፑኔ በ”ባዮቴክኖሎጂ” ትምህርት ነው። በዚህ ፕሮግራም ውስጥ በ”ጄኔቲክ ኢንጂነሪንግ” እና በእፅዋት “ቲሹ ካልቸር” ብዙ ልምድን አካብታለች። 

ቢልልኝ አማረ

የፊዚክስ ቪዲዮ ሌክቸረር

ቢልልኝ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚገኘው የሜካኒካል እና የኢንዱስትሪያል ኢንጂኒሪንግ ዲማርትመንት ሌክቸረር ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። በራያ ቆቦ ተወልዶ እ.አ.አ. በ2015 የመጀመሪያ ዲግሪውን እና በ2017 የማስተርስ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገኘ ሲሆን ያጠናውም ሜካኒካል ኢንጂኒሪንግ ነው። በበጣም ታልቅ ዲስቲንክሽን ተመርቆ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚሰጡ የፊዚክስ ትምህርትዎችን ከእ.አ.አ 2015 ጀምሮ ሌክቸር እያደረገ ይገኛል። 

ምህረት ገረመው

የሒሳብ ቪዲዮ ሌክቸረር

ምህረት የኮንክሪት ማቴርያል እና ስትራክቸርስ ተመራማሪ ስትሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሲቪል ምህንድስና የሁለተኛ ዲግሪዋን ተከታትላለች፡፡ በኢንደስትሪ እና በትምህርቱ ዘርፍ አስር ዓመት የሚጠጋ የስራ ልምድ ያላት ሲሆን ከሙያዊ ስራዋ በተጓዳኝ ማህበረሰብንና አካባቢን በተጨባጭ ሊጠቅሙ የሚችሉ ስራዎችን መስራት ላይ ታተኩራለች::

ዘካርያስ ተሾመ

የቪዲዮ ሌክቸረር - ሒሳብ

ዘካርያስ የአይቲ ባለሙያ ሲሆን ከኖርዌይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዲግሪ ያለው። በመስተንግዶ ኢንዱስትሪ ውስጥ እንደ አይሲቲ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ይሰራል።

​ምሩቅ አለሙ

ጊዜያዊ የኢትዮጵያ ፕሮግራምዎች ስራ አስፈፃሚ

ምሩቅ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ትምህርት ዘርፍ የሁለተኛ ዲግሪ የላት ሲሆን የልማት ፐሮጀክቶን የማስተባበር እና የመምራት  የ 10 አመት ልምድ አላት።በሆልት ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የፕሮግራም ሃላፊ፥ጊዜያዊ እና ምክትል የሀገር ውስጥ ተወካይ በመሆን ለ4 አመት አገልግላለች። በትምህርት እና በልጆች  እንክብካቤ ዙሪያ የመስራት ከፍተኛ ፍላጎት አላት።

ረዲኤት ታደሰ

የማርኬቲንግ እና ቴክኖሎጂ ሊድ

ሬድኤት በአዲስ አበባ የምትኖር ኢትዮጵያዊት ናት ፣በሲቪል ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪዋን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝታለች ፣ በአሁኑ ጊዜ የሁለተኝ ዲግሪ ትምህርትዋን በሶፍትዌር ምህንድስና በ HiLCoE School of Computer Science and Technology ተከታትላ የመመረቂያ ጽሁፍዋን በማዘጋጀት ላይ ነች፡፡

​አማካሪዎቻችን

ኔተን ስቶነር

የቦርድ ቼርማን እና አማካሪ

ሊና የድርጅቱ መስራች እና ዳይሬክተር ስትሆን አዲስ አበባ ውስጥ ነው ተውልዳ ያደገችው። የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪዎችዋን አሜሪካ በሚገኘው ዬል ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ያጠናቀቀችው በአሁኑ ሰዓት በቻይና ሀገር በቤጂንግ ከተማ ነው የምትኖረው። 

ቢኒያም አሰፋ ጥበቡ

አካዳሚክ አማካሪ