ችግርዎን እንረዳለን
እንደ ሒሳብ እና ፊዚክስ ያሉ ከባድ የትምህርት ዓይነትዎችን በደንብ በማይናገሩት ቋንቋ መማር ቀላል አይደለም።
ይህ “ሳቋማ” የተሰኘው ዌብሳይት፥ አፕሊኬሽን እና ዩትዩብ ቻናል ትምህርት ቤት የሚማሩት ትምህርት በቀላሉ እና በእራስዎ ቋንቋ እንዲገባዎ ያስችልዎታል። በራስዎ ጊዜ እና በራሳስዎ ፍጥነት ከእኛ ጋር ሆነው የትምህርት ችግርዎን ይቅረፉ።
የብዙ መፅሐፍዎችን ይዘት በቪዲዮ መልክ አዘጋጅተንልዎታል። ትምህርታችን በስዕል የተደገፈና ቀለል ባለ መልኩ የቀረበ ነው። ሳቋማ (ሳይንስ ቋንቋ ማትስ) እንደማለት ሲሆን እነዚህን ጠጣር ትምህርትዎች በደንብ ተንትኖ ያስረዳዎታል። በዩትዩብ ቻናላችን እና በአፕሊኬሽንአችን መጠቀምም ይችላሉ። አፕሊኬሽንአችን ላይ ያሉትን ቪዲዮዎች ከጫኑ በኋላ ያለ ኢንተርኔት መጠቀም ይችላሉ።
የቋንቋ ችግር እንዳለ ይገባናል
ከፍተኛ ትምህርትዎች በእንግሊዘኛ እንደሚሰጡ ይታወቃል። ነገር ግን ብዙዎቻችን በአካባቢያችን እንግሊዘኛ ተናጋሪዎች የሉም። ስለዚህ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክህልዎታችን ዝቅ ያለ ነው።
በመሆኑም የጥናት ጊዜአችን በጭንቀትና በራስ ያለመተማመን ስሜት የተሞላ ሊሆን ይችላል።
በትምህርት ጥሩ መሰረት አለመያዝ
ከባድ ትምህርትዎችን ከመሰረቱ ካልያዝናቸው ውስብስብ እና አስፈሪ ይሆናሉ።
በጊዜ እጥሮት ወይም በሀላፊነት ብዛት መማር ያለብንን ነገር አጣርተን ሳንማር ጊዜው ያልፋል። ቀናት ወደ ወራት፥ ወራት ደግሞ ወደ ዓመታት ተቀይረው ትምህርቱ ተወሳስቦ ቁጭ ይላል። እኛም ትምህርቱን እንፈራና “እኔ ትምህርት አይገባኝም” የሚል የተሳሳተ ሀሳብ ውስጥ እንገባለን።
እንርዳችሁ
በቀላሉ የሚገባ ትምህርት አቅርበንላቹሃል
ትምህርታችን በቪዲዮ መልክ የቀረበና በስዕል እና በጥሩ ምሳሌዎች የተደገፈ ነው። እንዲሁም በራስዎ ፍጥነት መማር ያስችልዎታል። ትንታኔው በአማርኛ ቋንቋ እንዲገባዎ ተደርጎ የተሰራ ቢሆንም አስፈላጊ ቃላትዎች እና የሳይንሳዊ አገላለፅዎች ግን በእንግሊዘኛም ቀርበዋል። ስለዚህ ትምህርት ቤት በእንግሊዘኛ በሚማሩበት ወቅት ድንግር አይልዎትም።
ህልምዎን እውን ያድርጉ
መጪው ጊዜዎ የተሳካ እንዲሆን እናግዝዎታለን
የልጅነት ህልም ያለ ትጋት እና ድካም እውን አይሆንም። ህልምን ለማሳካት ደግሞ ድጋፍ ያስፈልጋል። እኛ የሳቋማ ባለሞያዎች ልክ እንደ ትልቅ ወንድም፥ እህት ወይም አስጠኚ ሆነን ልናገለግልዎ ዝግጁ ነን። አንድ ላይ ሆነን ህልምዎን እውን እናድርግ!
አጋርዎቻችን
ከተለያዩ ተቋምዎች ጋር በመተባበር አላማችንን እውን ማድረግ
Khan Academy (ካን አካዳሚ) የተሰኘው በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነ የትምህርት ተቋም ነው። ሳቋማ የKhan Academy የትምህርት ይዘትዎችን ከኢትዮጵያ ካሪኩለም ጋር እያመሳከረ ያቀርብላቹሃል። የሳቋማ መምህርዎች የራሳቸውን የትምህርት ቪዲዮዎችን ከማዘጋጀታቸውም በላይ በተለይ የሒሳብ ትምህርት ላይ የKhan Academyን የአስተማመር ዘዴ ይጠቀማሉ። Khan Academy ለሚያደርግልን ድጋፍ ሁሉ እናመሰግናለን።
ማክሚላን ስትዋርት ፋውንዴሽንን ስላደረገለን የግራንት ድጋፍ እናመሰግናለን።
ሳቋማ ሁሌም ከእርስዎ ጋር ነው።
የቋንቋ፥ የሳይንስ እና የሒሳብ ትምህርትዎችን በተለያዩ ደረጃዎች አዘጋጅቶ ያቀርብልዎታል።
ከዚህ ዌብሳይትም በተጨማሪ የአንድሮይድ አፕሊኬሽን እና የዩትዩብ ቻናል አለን። አፕሊኬሽኑ የተለየ ጥቅም አለው። አፕሊኬሽኑ ላይ ያሉትን ቪዲዮዎች ከጫኑ በኋላ ያለ ኢንተርኔትም ቢሆን ማየት ይችላሉ።